ጠቅላላ ምልከታና ግብዣ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የእንስሳት ቁጥር ቢኖራትም ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል መጠቀም ባለመቻሏ እንደ እንዱስትሪ ውጤቶች ሁሉ የተወሰኑ የእንስሳት ተዋፅዖችን /ለምሳሌ ውተትና የወተት ተዋፅዖዎች/ ከውጭ ሀገራት እንድታስግባ ግድ ብሏታል። ለዚህም የተለያዩ ችግሮች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ ያህል ምንም እንኳ እንስሳቱ በተለያየ ስነምህዳር ተፈጥሯዊ ችግሮችን ተቋቁሞ የመኖር እምቅ አቅም ቢኖራቸውም ምርት የመስጠት አቅማቸው ዝቅተኛ መሆን፥ የተለያዩ በሽታዎች ተግዳሮት በየጊዜው መሰፊው መከሰትና ተቋማዊ የመከላከል አቅም ውስንነት መኖሩ እንዲሁም የመኖ አቅርቦትና ጥራት ስር የሰደዱ ችግሮች መሆናቸው ከዘርፉ የሚጠበቀውን ያህል ሀገሪቱ ሳትጠቀም ለመቅረቷ እንደምክንያት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ በእንስሳት ልማት ዘርፉ ተሳትፎ እጅግ ውስን መሆንና የአምራች፣ ምርትና ገበያ ትስስር ደካማ መሆን ከእንስሳቱ ከፍለ ኢኮኖሚ የሚጠበቀውን ያህል ለመጠቀም ማነቆ ሆኗል። ይህን ነበራዊ ሁኔታ በመረዳት እና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የናይል እንስሳት ሃብት ልማት አክስዮን ማህበር በመቋቋም ላይ የሚገኝ ሲሆን የእንስሳት ምርትንና ምርታማነትን ከማሳደግ ጀምሮ እስከ የአመራረት ሥርዓት እስከመቀየር ዓላማ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዓላማውን ተረድቶ የአክስዮን ዕጣዎችን በመግዛት የአክስዮን ማኅብሩ አባል እንዲሆን የአክስዮን ማህበሩ አደራጆች ይጋብዛሉ።
Copyright © 2022 NILE LIVESTOCK S.C. - All Rights Reserved.
Powered by GoDaddy